Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ጌቶቼ ሆይ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ ከዚያም እደሩ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁም ትሄዳላችሁ። እነርሱም፤ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ አይሆንም አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም፣ “ጌቶቼ፤ እባካችሁ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ ከዚያም እግራችሁን ታጠቡ፤ ዐድራችሁም ጧት በማለዳ ጕዟችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱም፣ “አይሆንም፤ እዚሁ አደባባይ ላይ እናድራለን” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባርያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፥ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፦ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ጌቶቼ ሆይ፥ ተቀብዬ ላስተናግዳችሁ ዝግጁ ነኝ፤ እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡ፤ እግራችሁንም ታጥባችሁ እዚሁ ዕደሩ፤ ጠዋት በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞአችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱ ግን “አይሆንም፤ እኛ እዚሁ በከተማይቱ አደባባይ እናድራለን” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 19:2
15 交叉引用  

ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤


ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ አለቸውም


እጅግም ዘበዝባቸው ወደ እርሱም አቀኑ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ።


እርሱም አለው፦ አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ግባ፤ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኔም ቤቱን ለግመሎችህም ስፍራ አዘጋጅቼአለሁ።


ስምዖንም አወጣላቸው። ሰውዮውም እነዚያን ስዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው ውኃ አመጣላቸው እግራቸውንም ታጠቡ ለአህዮቻቸው አበቅ ስጣቸው።


ዳዊትም ኦርዮን፦ ወደ ቤትህ ሂድ፥ እግርህንም ታጠብ አለው። ኦርዮም ከንጉሡ ቤት ሲወጣ ማለፊያ የንጉሥ መብል ተከትሎት ሄደ።


መጻተኛው ግን በሜዳ አያድርም ነበር፥ ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፥


ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ?


ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች።


በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።


እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።


跟着我们:

广告


广告