Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነርሱም ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። እርሱም፥ በድንኳኑ ውስጥ ናት አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እነርሱም አብርሃምን፣ “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “ድንኳን ውስጥ ናት” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነርሱም፦ “ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?” አሉት። እርሱም፦ “በድንኳኑ ውስጥ ናት” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነርሱም “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” አሉት። እርሱም “እዚያ ድንኳኑ ውስጥ ነች” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ሱም፥ “ሚስ​ትህ ሣራ ወዴት ናት?” አለው። እር​ሱም፥ “በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ናት” አለው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 18:9
8 交叉引用  

እርሱም፥ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኍላው ሳለች ይህንን ሰማች።


እርጎን ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር እነርሱም በሉ።


ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት ርብቃንም ወሰዳት ሚስትም ሆነችው ወደዳትም ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።


እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ ወዴት ነህ? አለው።


ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን ወደ ሁለቱም ባሪይዎች ድንኳን ገባ ነገር ግን አላገኘም።


እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፤ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ፤ አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም፤


ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤


跟着我们:

广告


广告