Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኍላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ትክክለኛና ጽድቅ የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 18:19
39 交叉引用  

ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤


የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።


እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቅለህ፥ አንተ ከአንተም በኍላ ዘርህ በትውልዳቸው።


የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካል፦ ቃሌን ሰምተሃልና።


ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ ልብሳችሁን፥ ለውጡ፤


የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና።


ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ባሪያህን ታውቃለህና ዳዊትስ ይናገርህ ዘንድ የሚጨምረው ምንድን ነው?


“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለላለም ይጥልሃል።


የእንግዶቹንም አማልክት መሠዊያ የኮረብታውንም መስገጃዎች አፈረሰ፤ ሐውልቶቹንም ሰበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤


አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ፥ አብራምን መረጥህ፥ ከዑር ከላውዴዎንም አወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም አልኸው፥


እኔ ዛሬ እንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፥ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል።


በእነዚያም ድንጋዮች ስፍራ ሌሌች ድንጋዮች ያገባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይመርጉታል።


እንዲህም ብሎአል፦ እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፥ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።


መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንድሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎቼ አኖራለሁ።


“ጠቦቶቼን ጠብቅ” አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ፦ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም፦ “በጎቼን አሰማራ።


ጳውሎስ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮቹ፦ “እነዚህ በመርከቡ ካልቆዩ እናንተ ትድኑ ዘንድ አትችሉም” አላቸው።


እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታኣ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።


ዲያቆናት ልጆቻቸውንና የራሳቸውን ቤቶች በመልካም እየገዙ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።


በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።


ሆኖም፦ ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።


እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።


ማኑሄም፦ ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድር ነው? የምናደርግለትስ ምንድር ነው? አለው።


跟着我们:

广告


广告