Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 17:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አብራምም በግምባሩ ወደቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አብራምም በግምባሩ ወደቀ፥ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “እነሆ፥ ቃል ኪዳኔ ከአንተ ጋር ነው፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አብራም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦

参见章节 复制




ዘፍጥረት 17:3
17 交叉引用  

አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፥ የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?


ዓይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ስዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ፥


ሕዝቡም ሁሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግምባራቸው ተደፍተው “እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው! እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው!” አሉ።


ደግሞም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብረሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን ሸፈነ።


በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደ ቀስተ ደመና አምሳያ፥ እንዲሁ በዙሪያው ያለ ፀዳል አምሳያ ነበረ። የእግዚአብሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። ባየሁም ጊዜ በግምባሬ ተደፋሁ፥ የሚናገርንም ድምፅ ሰማሁ።


እኔም ተነሥቼ ወደ ቈላው ሄድሁ፥ እነሆም፥ በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ክብር ያለ የእግዚአብሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፥ በግምባሬም ተደፋሁ።


ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ።


የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፥ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ።


ሙሴና አሮንም በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ፊት በግምባራቸው ወደቁ።


እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው፦ አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ ነፍስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።


ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅጽበት አጠፋቸዋለሁ። በግምባራቸውም ወደቁ።


ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።


እርሱም፦ አይደለሁም፥ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥


ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግምባራቸው ተደፉ።


跟着我们:

广告


广告