Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 12:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በምድርም ራብ ሆነ አብራንምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚያም ምድር ጽኑ ራብ ገብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አብራም ለጥቂት ጊዜ በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ወረደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በምድርም ራብ ሆነ፥ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በከነዓን ምድር ራብ ገባ፤ ራብም እየበረታ በመሄዱ አብራም የራቡን ጊዜ ለማሳለፍ በስተደቡብ ርቆ ወደ ግብጽ አገር ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 12:10
21 交叉引用  

በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር።


አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።


የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና።


ራብም በምድር ጸና።


በምድርም ሁሉ እህል አልነበረም ራብ እጅግ ጸንቶአልና ከራብም የተነሣ የግብፅ ምድርና የከነዓን ምድር ተጎዳ።


በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል ቀጥሎ ቀጥሎ ራብ ሆነ፥ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት አለ።


ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልገላ መጣ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ሎሌውንም “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያት ልጆችም ወጥ ሥራ፤” አለው።


በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ ከበቡአት።


ወደ ኤርምያስ ስለ ድርቅ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።


በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”


በግብፅና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፥ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም።


እንዲህም ሆነ፤ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告