Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 11:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን ተባለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያ እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለ ደበላለቀና እነርሱን በዓለም ዙሪያ ስለ በተናቸው የከተማውም ስም “ባቢሎን” ተባለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ባቢ​ሎን ተባለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ የም​ድ​ርን ቋንቋ ሁሉ ደባ​ል​ቆ​አ​ልና፤ ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ሁሉ ፊት ላይ እነ​ር​ሱን በት​ኖ​አ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 11:9
10 交叉引用  

የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን ኦሬክ አርካድ ካልኔ ናቸው።


የካም ልጆች በየነገድዳቸውና በየቋንቋቸው በየምድራችውን በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።


ለዔቦርን ሁለት ልጆች ተወለዱለት የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዩቅጣን ነው።


ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።


ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።


እንግዲህ ማኅበር ሁሉ አብረው ቢሰበሰቡ ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና ያልተማሩ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ፦ አብደዋል አይሉምን?


跟着我们:

广告


广告