Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 11:31 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፤ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ታራ ልጁን አብራምን፣ ሐራን የወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን እንዲሁም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ከዑር ዐብረው ወጡ፤ ነገር ግን ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 11:31
20 交叉引用  

የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ስረስ ነው ወደ ሰዶምና ወድደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣድረስ ነው።


የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።


አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ።


አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።


በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።


ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው።


ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል አሥር ግመሎችን ወስዶ ከጌትውም ዕቅ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ መስዼጦምይ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።


ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፤ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት


አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፤


ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።


አባቶቼ ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?


አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ፥ አብራምን መረጥህ፥ ከዑር ከላውዴዎንም አወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም አልኸው፥


እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።


አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን ካራንን፥ ራፍስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?


አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።


跟着我们:

广告


广告