Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 10:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከእነዚህም በባሕር ዳርቻ ሕዝቦች፥ ሁሉም በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፍለው የሚኖሩ የያፌት ልጆች ዘር ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከእ​ነ​ዚ​ህም የአ​ሕ​ዛብ ደሴ​ቶች ሁሉ በየ​ም​ድ​ራ​ቸው፥ በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ተከ​ፋ​ፈሉ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 10:5
26 交叉引用  

የካም ልጆች በየነገድዳቸውና በየቋንቋቸው በየምድራችውን በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው።


ለዔቦርን ሁለት ልጆች ተወለዱለት የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዩቅጣን ነው።


የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኍላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተክከፋፈሉ።


የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው።


የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፋጥ፥ ከነዓን ናቸው።


የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው ከእነርሱም ምድር ሁሉ ተሞካች።


ንጉሡም አርጤክስስ በምድርና በባሕር ደሴቶች ላይ ግብር ጣለ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል።


ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ፥ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።


እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፥ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።


ደሴቶች አይተው ፈሩ፥ የምድርም ዳርቾች ተንቀጠቀጡ፥ ቀረቡም ደረሱም።


ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።


በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፥ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።


ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፥ እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፥ አድምጡ፥ እግዚአብሔር ከማኅፀን ጠርቶኛል፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን አንስቶአል፥


ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፥ ማዳኔም ወጥቶአል፥ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፥ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፥ በክንዴም ይታመናሉ።


እንደ ሥራቸው መጠን እንዲሁ ቍጣን ለባላጋራዎቹ፥ ፍዳንም ለጠላቶቹ ይከፍላል፥ ለደሴቶችም ፍዳቸውን ይከፍላል።


እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።


ወደ ኪቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ፥ ወደ ቄዳርም ላኩና እጅግ መርምሩ፥ እንደዚህም ያለ ነገር ሆኖ እንደ ሆነ እዩ።


የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታትም ሁሉ፥ በባህር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥


ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላታል፦ የተወጉት ባንቋረሩ ጊዜ፥ በውስጥሽ እልቂት በሆነ ጊዜ፥ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች ይነዋወጡ የለምን?


አሁን በውድቀትሽ ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕርም ውስጥ ያሉ ደሴቶች ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።


ከዚህም በኋላ ፊቱን ወደ ደሴቶች ይመልሳል፥ ብዙዎችንም ይወስዳል፥ አንድ አለቃ ግን ስድቡን ይሽራል፥ ስድቡንም በራሱ ላይ ይመልሳል።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፥ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ 2 የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ 2 እንደ እስራኤል ልጆች ቁጥር 2 የአሕዛብን ድንበር አቆመ።


跟着我们:

广告


广告