Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊ​ትም ይለዩ ዘንድ ብር​ሃ​ናት በሰ​ማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለም​ል​ክ​ቶች፥ ለዘ​መ​ናት፥ ለዕ​ለ​ታት፥ ለዓ​መ​ታ​ትም ይሁኑ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 1:14
43 交叉引用  

እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሦስተኚ ቀን።


በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ።


በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።


ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።


በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?


እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።


አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፥ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፥


ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፥ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፥ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፥ አሕዛብ ይፈሩታልና።


ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል፥ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ፥ እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወራቱ እንዳይሆን የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያላጸናሁ እንደሆነ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ፥ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በመባቻ ቀን ይከፈት።


በመባቻም ቀን ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን፥ ነውር የሌለባቸውንም ስድስት ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቅርብ፥


ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።


ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ሰውረዋል።


ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥


በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በብርሃንም ቀን ምድሩን አጨልማለሁ።


ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥


በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥


የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ።


ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።


ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥


አራተኛውም መልአክ ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፥ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።


የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጕዱ ጢስ ጨለሙ።


跟着我们:

广告


广告