Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዕዝራ በመጀመሪያውም ወር በአንደኛው ቀን ከባቢሎን ሊወጣ ጀመረ፤ መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና በአምስተኛ ወር በመጀመሪያው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 መልካሚቱ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ስለ ነበረች፣ ከባቢሎን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ተነሥቶ በዐምስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ኢየሩሳሌም ደረሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በመጀመሪያው ወር በአንደኛው ቀን ከባቢሎን መውጣት ጀመረ፥ መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች በአምስተኛ ወር በመጀመሪያው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል በእርሱ ላይ ስለ ነበረ ከባቢሎን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ተነሥቶ ኢየሩሳሌም በአምስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ደረሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በአ​ን​ደ​ኛው ቀን ከባ​ቢ​ሎን ሊወጡ ጀመሩ፤ መል​ካ​ሚ​ቱም የአ​ም​ላኩ እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።

参见章节 复制




ዕዝራ 7:9
11 交叉引用  

ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው በሙሴ ሕግ ፈጣን ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።


በንጉሡም በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ።


በላያችንም መልካም በሆነው በአምላካችን እጅ ከእስራኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞሖሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሰራብያን፥ ከእርሱም ጋር አሥራ ስምንቱን ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን።


ንጉሡንም፦ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኃይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና።


በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም እንሄድ ዘንድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን፤ የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፤ በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን።


ወደ ኢየሩሳሌም ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ተቀመጥን።


የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።


በቤቱም አጠገብ ላለው ለግንብ በሮች፥ ለከተማውም ቅጥር፥ ለምገባበትም ቤት እንጨት እንዲሰጠኝ ለንጉሡ ዱር ጠባቂ ለአሳፍ ደብዳቤ ይሰጠኝ” አልሁት። ንጉሡም በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነችው እንደ አምላኬ እጅ ሰጠኝ።


ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፥ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።


跟着我们:

广告


广告