Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።”’

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይላል” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደው “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘በበረሓ ለእኔ በዓል ለማድረግ እንዲሄዱ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይልሃል” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”

参见章节 复制




ዘፀአት 5:1
26 交叉引用  

ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፥ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር በፈረሱ አመለጠ።


ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።


ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤


ሙሴም፦ “እኛ እንሄዳለን፤ የእግዚአብሔርም በዓል ሆኖልናልና ታናናሾቻችንና ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም፥ በጎቻችንና ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤” አለ።


እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገባላችሁ፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፤ አሁንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንሠዋ ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ።


አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው።


ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ’ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ”’ ትለዋለህ።


“ግባ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር”።


እነዚህ የእስራኤልን ልጆች “ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህ ሙሴና አሮን ናቸው።


እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆም እስከ ዛሬ አልሰማህም።


ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል።


እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “አሮንን፦ ‘በትርህን ዘርጋ፤ በግብፅም አገር ሁሉ ቅማል እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ፤’ በለው።”


እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፤ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግብፅ አገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቁም፤ እነሆ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


እኛስ ለእግዚአብሔር ለአምላካችን እንሠዋ ዘንድ እንደሚያዝዘን የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ እንሄዳለን፤” አለ።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገብተህ ንገረው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።


ልትለቅቃቸውም እንቢ ብትል ብትይዛቸውም፥


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።


አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ኵርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራቸው፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።


ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።”


ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም።


跟着我们:

广告


广告