Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 “በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፍት በኵርን ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ የእኔ ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከእስራኤላውያን መካከል የእናቱ የበኵር ልጅ የሆነው ማሕፀን ከፋች ሰውም ሆነ እንስሳ የእኔ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ማሕፀንን የሚከፈት በኩርን ሁሉ፤ በእስራኤል ልጆች መካከል፥ ከሰውም፥ ከእንስሳም ለእኔ ቀድስልኝ፥ የእኔ ነው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”

参见章节 复制




ዘፀአት 13:2
19 交叉引用  

በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኩራት፥ የበሬዎችቻችንንና የበጎቻችንን በኩራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ የእህላችንንም በኩራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገርው፦


ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብንም አለቃ አትርገመው።


የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።


ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤


ለእኔም የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ሠዋሽላቸው።


ልጆቼን አረድሽ፥ ለእነርሱም በእሳት በኩል አሳልፈሽ ሰጠሽ፥ በውኑ ግልሙትናሽ ጥቂት ነውን?


ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን የእንስሳ በኵራት ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።


ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ ማኅፀን የሚከፍት ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትቤዠዋለህ።


እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኵሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤


በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና ሌዋውያን ለእኔ ይሁኑ፤ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይቼአለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ላምህና በግህ የወለዱትን ተባት የሆነውን በኩራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ፤ በበሬህ በኩራት አትሥራበት፥ የበግህንም በኩራት አትሸልት።


በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥


跟着我们:

广告


广告