Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 11:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሙሴም አለ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በእኩል ሌሊት እኔ በግብፅ መካከል እወጣለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚህ በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘እኩለ ሌሊት ሲሆን በመላው የግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በእኩለ ሌሊት እኔ በግብጽ መካከል እወጣለሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በእኩለ ሌሊት በግብጽ ምድር እዘዋወራለሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሙሴም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ኩለ ሌሊት እኔ በግ​ብፅ መካ​ከል እገ​ባ​ለሁ፤

参见章节 复制




ዘፀአት 11:4
12 交叉引用  

በሾላውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ፥ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ለመምታት በፊትህ ወጥቶ ይሆናልና በዚያን ጊዜ ቸኩል አለው።


እነርሱ በመንፈቀ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ እጅ ይነጠቃሉ።


እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፤ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በደጁ ላይ ያልፋል፤ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተውም።


እንዲህም ሆነ፤ እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በግዞት እስካሉት እስከ ምርኮኞቹ በኵር ድረስ፥ የግብፃውያንን በግብፅ ምድር የተገኘውን በኵር ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵሮች ሁሉ መታ።


እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፥ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።


በግብጽ እንደ ነበረው ቸነፈርን ሰደድሁባችሁ፥ ጐበዛዝቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሰፈራችሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ አወጣሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶ ይሆናል፥ ይላል እግዚአብሔር።


ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።


እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告