Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን መልሶ አስመጣቸው፤ ሂዱ፤ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን እንዲመጡ ተደረገ፤ “ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሙሴንና አሮንን ወደ ፈርዖን አመጡአቸው፦ “ሂዱ፥ ጌታ አምላካችሁን አገልግሉ፥ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ሙሴና አሮን ተጠርተው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም “ሄዳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን ማገልገል ትችላላችሁ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ወደ ፈር​ዖን ጠሩ​አ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?”

参见章节 复制




ዘፀአት 10:8
6 交叉引用  

ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ፦ “ሂዱ፤ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁ ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሂዱ፤” አለው።


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ፥ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ፤


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፤ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ።


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጕንቸሮቹን ከእኔ ከሕዝቤም እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እለቅቃለሁ፤” አላቸው።


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ በአገሩ ውስጥ ለአምላካችሁ ሠዉ፤” አላቸው።


የአምላክ ነጎድጓድ በረዶውም በዝቶአልና ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፤ እለቅቃችሁማለሁ፤ ከዚያም በኋላ በዚህ አትቀመጡም፤” አላቸው።


跟着我们:

广告


广告