Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ እያስጨነቁ የግዳጅ ሥራ የሚያሠሯቸውን አሠሪ አለቆች ሾሙባቸው። እስራኤላውያንም ፊቶምና ራምሴ የተባሉ ንብረት ማከማቻ ከተሞችን ለፈርዖን ሠሩለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በብርቱ ሥራ እንዲያስጨንቁአቸው ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራዓምሴስን የማከማቻ ከተሞች አድርገው ሠሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።

参见章节 复制




ዘፀአት 1:11
21 交叉引用  

አብራምንም አለው፤ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው።


ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ።


ቤንሀዳድ ንጉሡን አሳን“እሺ” አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰደደ፤ እነርሱም ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ መቱ።


በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን ከተሞች ሁሉ ሠራ።


በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም፥ በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።


በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፤ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው የወንድሞቹን የዕብራውያንን ሰው ሲመታ አየ።


እግዚአብሔርም አለ፦ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፤ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


የሕዝቡም አስገባሪዎች ሹማምቶቹም ወጡ፤ ሕዝቡንም፥ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ገለባ አልሰጣችሁም።


የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን መጡ፤ “ለምን በባሪያዎችህ እንዲህ ታደርጋለህ?


ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቁጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፥ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮኻሉ።


አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወረዱ፥ በግብፅም እጅግ ዘመን ተቀመጥን ግብፃውያንም እኛንና አባቶቻችንን በደሉ፤


ግብፃውያንም ክፉ ነገር አደረጉብን፥ አስጨነቁንም፥ በላያችንም ጽኑ ከባድ ሥራን ጫኑብን፤


跟着我们:

广告


广告