Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኀጥእ መቶ ወንጀል ሠርቶ ዕድሜው ቢረዝምም፣ አምላክን የሚያከብሩ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው ሰዎች መልካም እንደሚሆንላቸው ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት መልካም እንደሚሆን አውቃለሁ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይኸውም ኃጢአተኞች መቶ ጊዜ ወንጀል ቢሠሩም ለረጅም ዘመን ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያከብሩ ሁሉ ነገር እንደሚሰምርላቸው ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤

参见章节 复制




መክብብ 8:12
34 交叉引用  

አንተም ቀድሞ እንደ ጠፋብህ ሠራዊት፥ ፈረሱን በፈረስ ፋንታ፥ ሰረገላውንም በሰረገላ ፋንታ፥ ሠራዊትን ቍጠር፤ በሜዳም ላይ ከእነርሱ ጋር እንዋጋለን፥ በእርግጥም እንበረታባቸዋለን። ምክራቸውንም ሰማ፥ እንዲሁም አደረገ። ፕ


ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ፤ ዓለሙም እንዳይናወጥ ጸንቶአል።


አሁን ግን በቍጣው አልጐበኘምና፦ በኃጢአት እጅግ አያስብም ትላለህ።


እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፤ እጅግም በረታ።


የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።


እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ፥ ሊጨመርበት ወይም ከእርሱ ሊጐድል አይቻልም፥ እግዚአብሔርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደረገ።


ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፥ እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፥ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድር ነው?


ብዙ ሕልም ባለበት ዘንድ፥ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ስፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ፥ አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ።


ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ ኀጥእም በክፋቱ እጅግ ዘመን ሲኖር፥ ይህን ሁሉ ከንቱ በሆነ ዘመኔ አየሁ።


እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣልና ይህን ብትይዝ ከዚያም ደግሞ እጅህን ባታርቅ መልካም ነው።


እስከ ዛሬ ድረስ አልተዋረዱም አልፈሩምም፥ በእናንተና በአባቶቻችሁም ፊት ባኖርሁት ሕጌና ሥርዓቴ አልሄዱም።


ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።


ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።


ነገር ግን እግዚአብሔር ቍጣውን ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ፥ አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለ ጠግነት ይገልጥ ዘንድ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ከቻለ፥ እንዴት ነው?


በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው።


በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።


ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ለዘላለም በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዝህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቅ።


ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤


跟着我们:

广告


广告