Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በአፍህ አትፍጠን፤ በአምላክም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ አምላክ በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፥ እንዲሁም የአላዋቂም ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከመናገርህ በፊት አስብ፤ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት በችኰላ ስእለት አታድርግ፤ እግዚአብሔር በሰማይ አንተ ግን በምድር መሆንህን በማሰብ የምትናገረው ቃል የተመጠነ ይሁን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ፥ አን​ተም በም​ድር ነህና በአ​ፍህ አት​ፍ​ጠን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቃልን ይና​ገር ዘንድ ልብህ አይ​ቸ​ኩል፤ ስለ​ዚ​ህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።

参见章节 复制




መክብብ 5:2
21 交叉引用  

አብርሃምም መለስን አለም፤ እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤


እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ።


እርሱም፥ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት ከዚያ አሥር አላጠፋትም አለ።


ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ


ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።


የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፥ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።


የአፉ ቃል መጀመሪያ ስንፍና ነው፥ የንግግሩ ፍጻሜም ክፉ እብደት ነው።


ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፥ እንዲሁም የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል።


ብዙ ሕልም ባለበት ዘንድ፥ እንዲሁም ደግሞ ብዙ ቃል ባለበት ስፍራ በዚያ ብዙ ከንቱ ነገር አለ፥ አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ።


ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።


ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ክፉን ወይም መልካምን ያደርግ ዘንድ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፤ ሳያስብ የማለው ስለ ማናቸውም ነገር ቢሆን፤ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል።


አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።


እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥


የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት።


ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


ዮፍታሔም፦ በእውነት የአሞንን ልጆች በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥


跟着我们:

广告


广告