Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዓይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ ብቸኛ ሰው አለ፤ ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤ እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው? ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።

参见章节 复制




መክብብ 4:8
21 交叉引用  

እግዚእብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረት እንፍጠርለት።


ከሰማይም በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋሁ፥ እግዚአብሔር ይደክሙባት ዘንድ ይህችን ለሰው ልጆች የሰጠ ክፉ ጥረት ናት።


ነገር ሁሉ ያደክማል፥ ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም፥ ዓይን ከማየት አይጠግብም፥ ጆሮም ከመስማት አይሞላም።


ሰው በጥበብና በእውቀት በብልሃትም ከደከመ በኋላ ለሌላ ላልደከመበት ሰው ያወርሰዋልና፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ትልቅም መከራ ነው።


ዘመኑ ሁሉ ኀዘን፥ ጥረትም ትካዜ ነው፥ ልቡም በሌሊት አይተኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ከንቱ ነገር አየሁ።


ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፥ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


በጠቅላላው ግን የአገሩ ጥቅም እርሻን የሚወድድ ንጉሥ ቢኖር ነው።


ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻን ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!


ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው።


跟着我们:

广告


广告