Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፥ አዝማሪዎችንና አርሆዎችን የሰዎች ልጆችንም ተድላ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ለራሴም ብርንና ወርቅን፣ የነገሥታትና የአውራጃዎችን ሀብት አካበትሁ፤ ወንድና ሴት አዝማሪዎች፣ የሰው መደሰቻ የሆኑ ቅምጦች ነበሩኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችን፥ ለሰዎች ልጆች ተድላ የሚሰጡ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እኔ በምገዛው አገር ሁሉ ከልዩ ልዩ አውራጃዎች የከበሩ የቤተ መንግሥት መዛግብትን በመሰብሰብ ብዙ ወርቅና ብር አከማቸሁ፤ እኔን የሚያሞግሡ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችንም አዘጋጀሁ፤ ለሰው ተድላና ደስታን ሊሰጡ የሚችሉ እጅግ ብዙ ሴቶችንም ሰበሰብኩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።

参见章节 复制




መክብብ 2:8
21 交叉引用  

ዛሬ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፥ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ የምበላውንና የምጠጣውን ጣዕሙን መለየት እችላለሁን? የወንዱንና የሴቲቱን ዘፈን ድምፅ መስማት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን እከብድብሃለሁ?


ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።


ግብርም የሚያስገብሩ ሰዎች ነጋዴዎችም የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድርም ሹማምት ከሚያወጡት ሌላ፥ በየዓመቱ ለሰሎሞን የሚመጣለት የወርቅ ሚዛን ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበረ።


ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር የተባለውም ቤት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ እንጂ ብር አልነበረም። በሰሎሞን ዘመን ብር ከቶ አይቆጠርም ነበር።


ለእርሱም ወይዛዝርት የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።


ንጉሡም ሮብዓም በፋንታው የናስ ጋሾችን ሠራ፤ የንጉሥንም ቤት ደጅ በሚጠብቁ በዘበኞች አለቆች እጅ አኖራቸው።


ኪራምም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ለንጉሡ ላከ።


ወደ ኦፊርም መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሰሎሞን ይዘው መጡ።


ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ ከአባታቸው እጅ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።


ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።


ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።


አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፥ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፥ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።


የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።


ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።


በመሰንቆም ድምፅ ለምትንጫጩ፥ እንደ ዳዊትም የዜማን ዕቃ ለምታዘጋጁ፥


跟着我们:

广告


广告