Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወደ አደባባይ የሚያወጡ በሮች ሲዘጉ፣ ወፍጮ ሟልጦ ድምፁ ሲላሽ፣ ሰው በወፍ ድምፅ ሲነሣ፣ ዝማሬው ሁሉ ሲዳከም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ጆሮችህ የአደባባይ ጫጫታ አይሰሙም የወፍጮ ወይም የሙዚቃ ድምፅ መስማት ይሳንሃል፤ ሆኖም የወፍ ድምፅ እንኳ ከእንቅልፍህ ይቀሰቅስሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ደጆቹ በሚ​ዘ​ጉ​በት ቀን፥ የወ​ፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከዎፍ ድምፅ የተ​ነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚ​ጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤

参见章节 复制




መክብብ 12:4
5 交叉引用  

ዛሬ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፥ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ የምበላውንና የምጠጣውን ጣዕሙን መለየት እችላለሁን? የወንዱንና የሴቲቱን ዘፈን ድምፅ መስማት እችላለሁን? እኔ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን እከብድብሃለሁ?


በአንገቱ ኃይል ታድራለች፥ ግርማ በፊቱ ይዘፍናል።


ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፥ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣይው፥ ባትሽን ግለጪ፥ ወንዙን ተሻገሪ።


ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ።


በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥


跟着我们:

广告


广告