Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አንተም የምታውቃቸው ስለ እነርሱም፦ በዔናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይችላል? ሲባል የሰማኸው ታላቁና ረጅሙ ሕዝብ የዔናቅ ልጆች ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዔናቃውያን ብርቱና ቁመተ ረዣዥም ሕዝቦች ናቸው፤ ስለ እነርሱ ታውቃለህ፤ “ዔናቃውያንን ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?” ሲባልም ሰምተሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ስለ እነርሱም፥ ‘በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል?’ ሲባል የሰማኸው፥ አንተም የምታውቃቸው፥ ግዙፍና ረጃጅም ሕዝቦች የዔናቅ ልጆች ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ግዙፋን የሆኑ ቁመተ ረጃጅሞችና ብርቱዎች ናቸው፤ እነርሱም ‘ማንም ሊቋቋማቸው የማይችል የዔናቅ ዘሮች ናቸው’ ሲባል ሰምተሃል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አን​ተም የም​ታ​ው​ቃ​ቸው፥ ስለ እነ​ር​ሱም፦ በዔ​ናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይች​ላል? ሲባል የሰ​ማ​ኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔ​ናቅ ልጆች ናቸው።

参见章节 复制




ዘዳግም 9:2
16 交叉引用  

እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው?


ጠንቍዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል በጠንቍዮችና በግብፃያን ሁሉ ላይ ነበረና።


በእርሱም ላይ የሚመጣው ግን እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ በፊቱም የሚቆም የለም፥ በመልካሚቱም ምድር ይቆማል፥ በእጁም ውስጥ ጥፋት ይሆናል።


አውራውም በግ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ፥ አራዊትም ሁሉ ይቋቋሙት ዘንድ አልቻሉም፥ ከእጁም የሚያድን አልነበረም፥ እንደ ፈቃዱም አደረገ፥ ራሱንም ታላቅ አደረገ።


እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ኮምበል ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፥ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።


በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎእ በፊት ሰባት ዓመት ተሠርታ ነበር።


ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም የጸኑ ናቸው፤ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን።


በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፥ የዔናቅን ልጆች፥ አየን፤ እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ።


ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።


ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።


ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም በፊትህ ይቆም ዘንድ አይችልም።


በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፥ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።


በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።


ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ አሳደደ።


跟着我们:

广告


广告