Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እንግዲህ በእነርሱ ላይ የምታደርጉት ይህ ነው፤ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የአሼራ ምስል ዐምዶቻቸውን ቍረጡ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም አድቅቁት፥ የእነርሱንም አሼራ ሰባብሩ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ነገር ግን በእነርሱ ላይ የምታደርጉት እንደዚህ ነው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፍርሱ፤ ከድንጋይ የተሠሩ የጣዖት ማምለኪያ ዐምዶቻቸውንም እያንከታከታችሁ ጣሉ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሰባብሩ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።

参见章节 复制




ዘዳግም 7:5
16 交叉引用  

ከበኣልም ቤት ሐውልቶቹን አወጡ፤ አቃጠሉአቸውም።


አማልክቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትም አዘዘ፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው።


የእንግዶቹንም አማልክት መሠዊያ የኮረብታውንም መስገጃዎች አፈረሰ፤ ሐውልቶቹንም ሰበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤


ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፥ አታምልካቸውም፤ እንደ ሥራቸውም አትሥራ፤ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብራቸው።


የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣው።


ነገር ግን መሠዊያዎቻቸውን ታፈርሳላችሁ፥ ሐውልቶቻቸውንም ትሠብራላችሁ፥ የማምለኪያ ዓፀዶቻቸውንም ትቈርጣላችሁ፤


እጁም የሠራችውን መሠዊያ አይመለከትም፥ ጣቶቹም ወደ አበጁአቸው፥ ወደ ማምለኪያ ዐፀዶች ወይም ወደ ፀሐይ ምስሎች፥ አያይም።


እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።


የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤


ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል።


አምላክህ እግዚአብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም።


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።


跟着我们:

广告


广告