Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 7:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንዳይከተለኝ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምክንያቱም እኔን ከመከተል ልጆችህን መልሰው ሌሎችን አማልክት እንዲያመልኩ ስለሚያደርጉና ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቍጣ በላይህ ነድዶ፣ ፈጥኖ ስለሚያጠፋህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እኔን እንዳይከተል፥ ሌሎችንም አማልክት እንዲያመልክ ልጅህን ያስታልና፤ ያኔ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ፈጥኖም ያጠፋችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይህን ብታደርግ ልጆችህን ከእግዚአብሔር አስኰብልለው ባዕዳን አማልክትን እንዲከተሉ ያደርጉአቸዋል፤ ይህም ከሆነ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ተቈጥቶ ወዲያው ያጠፋሃል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ልጅ​ህን ከእኔ ያር​ቀ​ዋ​ልና፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ያመ​ል​ካ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፤ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ች​ኋል።

参见章节 复制




ዘዳግም 7:4
14 交叉引用  

በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ ታናሽ ነገር መሰለው፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢያት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥


ሴት ልጆቻቸውንም ከወንድ ልጆችህ ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።


ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረጅም ዘመን አትቀመጡባትም።


በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መጡ፥


እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ ብትጠጉ፥ ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ እናንተም ወደ እነርሱ እነርሱም ወደ እናንተ ብትደራረሱ፥


የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ።


የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ እንዲህም አለ፦ ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው ያዘዝሁትን ቃል ኪዳን ስለ ተላለፉ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ አባቶቻቸውም እንደ ጠበቁ፥


ሴት ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፥ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፥ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ።


跟着我们:

广告


广告