Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእነርሱም ጋር አትጋባ፤ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ፥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከእነርሱ ጋራ ጋብቻ አታድርግ፤ ሴት ልጆችህን ለወንድ ልጆቻቸው አትስጥ፤ ወይም ለወንድ ልጆችህ ሴት ልጆቻቸውን አታምጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከእነርሱም ጋር አትጋባ፥ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ፥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከእነርሱ አትጋባ፤ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ልጆችህ ከእነርሱ ማንንም እንዲያገቡ አትፍቀድላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አት​ጋባ፤ ሴት ልጅ​ህን ለወ​ንድ ልጁ አት​ስጥ፥ ሴት ልጁ​ንም ለወ​ንድ ልጅህ አት​ው​ሰድ።

参见章节 复制




ዘዳግም 7:3
14 交叉引用  

እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤


እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፤ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ፤” ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ።


በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ ታናሽ ነገር መሰለው፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።


አሁንም እንደ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ እንደሚፈሩት ምክር፥ ሴቶችን ሁሉ ከእነርሱም የተወለዱትን እንሰድድ ዘንድ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፤ እንደ ሕጉም ይደረግ።


ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፥


አባቱና እናቱም፦ ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለማግባት ትሄድ ዘንድ ከወንድሞችህ ሴቶች ልጆች ከሕዝቤም ሁሉ መካከል ሴት የለምን? አሉት። ሶምሶንም አባቱን፦ ለዓይኔ እጅግ ደስ አሰኝታኛለችና እርስዋን አጋባኝ አለው።


跟着我们:

广告


广告