Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዛ፥ ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈስሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነዚህን ሕግጋት አድምጡ! ታዘዙላቸውም! ይህን ብታደርጉ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በማርና በወተት በበለጸገች በዚያች ለም ምድር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንላችኋል፤ ትበዛላችሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፦ ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጥህ ዘንድ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ እጅግ እን​ድ​ት​በዛ፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ጠብቅ።” ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድረ በዳ ያዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ይህ ነው።

参见章节 复制




ዘዳግም 6:3
25 交叉引用  

ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤


ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል።


ወደ ሜዳም አወጣውና፥ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቆጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቁጠርን አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው


በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፦ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር እንዳል አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤


ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ ይባረላሉ፤


ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።


የእስራኤልም ልጆች ፍሬን አፈሩ፤ እጅግም በዙ፤ ተባዙም፤ እጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።


ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ፤ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ፤’ በላቸው።


ደግሞም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብረሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን ሸፈነ።


ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁ፥


የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉና ጻድቁን፦ መልካም ይሆንልሃል በሉት።


የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን አሉት።


ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፥ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።


እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብፅ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብፅ በዙ።


ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ጐብኝ፥ ሕዝብህንም እስራኤልን ለአባቶቻችን እንደ ማልህላቸው የሰጠኸንንም ወተትና ማር የምታፈስሰውን አገር ባርክ።


ወደዚህም ስፍራ አገባን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን።


የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ትገባ ዘንድ በተሻገርህ ጊዜ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ጻፍባቸው።


ለአባቶቻቸው ወደ ማልሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደ ምታፈስሰው ምድር ካገባኋቸው በኋላ፥ ከበሉም ከጠገቡም ከደነደኑም በኋላ፥ ሌሎችን አማልክት ተከትለው ያመልካሉ፥ እኔንም ይንቃሉ፥ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።


ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ለዘላለም በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዝህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቅ።


ጠብቁአት አድርጉአትም፤ ይህችን ሥርዓት ሁሉ ሰምተው፦ በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤


ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፥


跟着我们:

广告


广告