Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 5:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከእንግዲህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ብንሰማ እንሞታለን፤ ይህችም ታላቅ እሳት ፈጽማ ታጠፋናለች፤ ታዲያ ለምን እንሙት?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና፥ እንግዲያውስ አሁን ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የጌታን ድምፅ ደግመን ከሰማን እንሞታለን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ነገር ግን ያ ብርቱ እሳት ያጠፋናል፤ ታዲያ ለምን መሞት እንፈልጋለን? እግዚአብሔር አምላካችን እንደገና ቢናገረን እንሞታለን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አሁ​ንም አን​ሙት፤ ይህ​ችም ታላቅ እሳት አታ​ጥ​ፋን፤ እኛ የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ዳግ​መኛ ብን​ሰማ እን​ሞ​ታ​ለን።

参见章节 复制




ዘዳግም 5:25
12 交叉引用  

እርሱም አለ፦ በገነት ድምጽህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም።


ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበደበዱ፥ ርቀውም ቆሙ።


ሙሴንም፦ አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን አሉት።


ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።


እግዚአብሔርም አለኝ፦ የተናገሩት መልካም ነው፤


እንዲህም አለ፦ 2 እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ 2 በሴይርም ተገለጠ፤ 2 ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ 2 ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ 2 በስተቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።


አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውዬውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።


ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤


አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


跟着我们:

广告


广告