Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ ጠብቅ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ አክብረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ እንድትቀድሰው፥ የሰንበትን ቀን ጠብቅ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዝኩህ የሰንበትን ቀን ጠብቅ፤ ቀድሰውም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ዕለተ ሰን​በ​ትን ጠብቅ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘ​ህም ቀድ​ሳት።

参见章节 复制




ዘዳግም 5:12
11 交叉引用  

በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው።


እርሱም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው።


የእስራኤልም ወገን ስሙን መና ብለው ጠሩት፤


ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ።


ስድስት ቀን ሥራን ሥራ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።


ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፥


ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቅድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥


ከቤቶቻችሁም በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፥ ሥራንም ሁሉ አትሥሩበት፥ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁ የሰንበትን ቀን ቀድሱ።


ደግሞ፦ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤


ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥


跟着我们:

广告


广告