Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 4:39 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቅ፥ በልብህም ያዝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እንግዲህ በላይ በሰማይ፣ በታችም በምድር እግዚአብሔር እርሱ አምላክ መሆኑን ዛሬ ዕወቅ፤ በልብህም ያዘው፤ ሌላም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 እንግዲህ፥ ጌታ በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፥ በልባችሁም ያዙት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ስለዚህም በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር እግዚአብሔር እርሱ ብቻ አምላክ መሆኑንና ያለ እርሱ ሌላ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ በልባችሁም ያዙት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ በታ​ችም በም​ድር አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደ ሌለ ዛሬ ዕወቅ፤ በል​ብ​ህም ያዝ።

参见章节 复制




ዘዳግም 4:39
24 交叉引用  

ስለዚህም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ የለምና፥ በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለምና አንተ ታላቅ ነህ።


አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም።


“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለላለም ይጥልሃል።


አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፤ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።


እንዲህም አለ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ! በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ችሎታ በእጅህ ነው፤ ሊቍቍምህም የሚችል የለም።


እርሱም “ነገ” አለ። ሙሴም “አምላካችንን እግዚአብሔርን የሚመስል እንደሌለ ታውቅ ዘንድ እንደ ቃልህ ይሁን።


በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፥ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም አላስተዋለም።


ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፥ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።


አትፍሩ አትደንግጡም፥ ከጥንቱም ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም፥ ማንንም አላውቅም።


መሰንቆና በገና ከበሮና እምብልታም የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፥ እጁም ያደረገችውን አላስተዋሉም።


በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፥ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም።


እኔም ክፋታቸውን ሁሉ እንዳሰብሁ በልባቸው አያስቡም፥ አሁንም ሥራቸው ከብባቸዋለች፥ በፊቴም አለች።


እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።


ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።


እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ 2 ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።


አእምሮ ቢኖራቸው፥ 2 ይህንን ያስተውሉ ነበር፥ 2 ፍጻሜያቸውንም ያስቡ ነበር።


እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።


እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤


አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤


ይህንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀረለትም።


እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፥ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።


跟着我们:

广告


广告