Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 4:32 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረው ጀምሮ፥ ከሰማይ ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቃ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደሆነ ከአንተ በፊት የነበረውን የቀደመውን ዘመን ጠይቅ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን ጀምሮ እናንተ ከመኖራችሁ በፊት ስለ ነበረው የቀድሞ ዘመን ጠይቁ፤ ከአንዱ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው የሰማይ ጫፍ ድረስ ጠይቁ፤ እንደዚህ ያለ ታላቅ ነገር ከቶ ተደርጎ ወይስ እንደዚህ ዐይነት ነገር ከቶ ተሰምቶ ያውቃልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረው ጊዜ ጀምሮ፥ ከሰማይ ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደሆነ ከአንተ በፊት የነበረውን የቀደመውን ዘመን ጠይቅ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 “እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ጊዜ አንሥቶ እናንተ ከመወለዳችሁ በፊት በነበረው ዘመን ያለፈውን ነገር ሁሉ እስቲ መርምሩ፤ ምድርን በሞላ መርምሩ፤ ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ታላቅ ነገር ከቶ ተደርጎ ያውቃልን? እንደዚህ ያለውን ነገር የሰማ ከቶ አለ ይሆን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን በም​ድር ላይ ከፈ​ጠ​ረው ጀምሮ፥ ከሰ​ማይ ዳር እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ከቶ እን​ዲህ ያለ ታላቅ ነገር ሆኖ፥ ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰ​ምቶ እንደ ሆነ ከአ​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ጠይቅ።

参见章节 复制




ዘዳግም 4:32
15 交叉引用  

እግዚአብሔርም ሰዉን በመልኩ ፈጠረ በእግአብሔር መልክ ፈጠራቸዉ።


ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?


ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና እኛ የትናንት ብቻ ነን፥ ምንም አናውቅም፥ ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥ አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ፥


እርሱም አለው፦ እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉ፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ተአምራት በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤ እኔም በአንተ ዘንድ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና አንተ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል።


እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፥ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።


እናንተ ሽማግሌዎች፥ ይህን ስሙ፥ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፥ አድምጡ። ይህ በዘመናችሁ ወይስ በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ነበርን?


እንዲህም ብሎአል፦ እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፥ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።


በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።


እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን፥ ታመልካለህ።


ሰዎችህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ፈልሰው እንደ ሆነ አምላክህ እግዚአብሔር ከዚያ ይሰበስብሃል፥ ከዚያም ያመጣሃል።


የዱሮውን ዘመን አስብ፥ 2 የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ 2 አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ 2 ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። 2


እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ 2 በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? 2 እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ 2 የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። 2 ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ 2 አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።


አምላካችን እግዚአብሔር በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደሚቀርበን፥ አምላኩ ወደ እርሱ የቀረበው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?


跟着我们:

广告


广告