Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 33:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝቡንም ወደዳቸው፤ 2 ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ 2 በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ 2 ቃሎችህን ይቀበላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በርግጥ ሕዝቡን የምትወድድ አንተ ነህ፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው። ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤ ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በእርግጥ ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጁ ናቸው፤ እነርሱም በእግሮችህ ሥር ይሰግዳሉ፤ መመሪያህንም ከአንተ ይቀበላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር በእውነት ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑን ሁሉ ይጠብቃል፤ እነርሱም በእግሩ ሥር ተንበርክከው ይሰግዳሉ፤ መመሪያውንም ይቀበላሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ላ​ቸው፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ ከእ​ጅህ በታች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የአ​ንተ ናቸው። ቃሎ​ች​ህ​ንም ይቀ​በ​ላሉ።

参见章节 复制




ዘዳግም 33:3
31 交叉引用  

ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው።


ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ፥ እንዲህም በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።


እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፥ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።


ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘላለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፥ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።


እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።


ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ፥


ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።


ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።


ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤


የሆነውን ነገር ሊያዩ ወጥተውም ወደ ኢየሱስ መጡ፥ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ ልቡም ተመልሶ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።


እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ


አባቶችህን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ ከአንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ።


አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት።


ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤


እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።


እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፥ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።


跟着我们:

广告


广告