Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 3:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እግዚአብሔር ግን በእናንተ ምክንያት ተቆጣኝ አልሰማኝምም፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይበቃሃል፤ በዚህ ነገር ደግመህ አትናገረኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እግዚአብሔር ግን በእናንተ ሰበብ ተቈጥቶኝ ነበርና አልሰማኝም፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ይበቃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ስለዚህ ነገር አታንሣብኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 “ጌታ ግን በእናንተ ምክንያት ተቆጥቶኝ ነበር፥ አልሰማኝምም፥ ጌታም አለኝ፦ ‘እንግዲህ ይበቃሃል፤ በዚህ ጉዳይ ዳግመኛ አትናገረኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 “ነገር ግን በእናንተው በሕዝቡ ምክንያት እግዚአብሔር ተቈጣኝ፤ ልመናዬንም ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም በዚህ ፈንታ እንዲህ አለኝ፤ ‘እንግዲህስ በቃህ! ዳግመኛ ይህን ነገር አታንሣ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ አል​ሰ​ማ​ኝ​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘ይበ​ቃ​ሃል፤ በዚህ ነገር ደግ​መህ አት​ና​ገ​ረኝ።’

参见章节 复制




ዘዳግም 3:26
15 交叉引用  

“ሂድ፤ ለባሪያዬ ለዳዊት ንገረው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም።


ኢየሱስ ግን መልሶ፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አለ። እንችላለን አሉት።


ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፦ አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።


ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።


እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት በእኔ ተቆጣ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም፤


አላቸውም፦ እኔ ዛሬ መቶ ሀያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል።


እግዚአብሔርም፦ ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፤ በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም አለው።


跟着我们:

广告


广告