Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 3:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በዚያም ዘመን እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ መሣሪያችሁን ይዛችሁ እናንተ አርበኞች ሁሉ በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በዚያ ጊዜ እኔ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ለእናንተ ሰጥቷችኋል፤ ይሁን እንጂ የአካል ብቃት ያላቸው ሰዎቻችሁ ሁሉ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ፊት በመቅደም መሻገር አለባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “በዚህም ጊዜ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ይህን ምድር ትወርሱ ዘንድ ሰጥቶአችኋል፤ እንግዲህ የጦር ሰዎቻችሁን አስታጥቃችሁ ሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ምድራቸውን እስኪወርሱ ድረስ እነርሱን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው እንዲዘምቱ አድርጉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ምድር ርስት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን ይዛ​ችሁ እና​ንተ አር​በ​ኞች ሁሉ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制




ዘዳግም 3:18
18 交叉引用  

ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው።


ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም።


በምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ለመውረስ በሰጣችሁ አገር፥ የምትጠብቁአትና የምታደርጉአት ሥርዓትና ፍርድ እነዚህ ናቸው።


አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሰጠህ ምድር ላይ እግዚአብሔር በእውነት ይባርክሃልና አንተም የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ታደርጋትም ዘንድ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በመካከልህ ድሃ አይኖርም።


አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር በምትወርሳት ርስትህ የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።


አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ በምድርህ መካከል ሦስት ከተሞችን ለራስህ ትለያለህ።


ስለዚህ እኔ፦ ለአንተ ሦስት ከተሞችን ለይ ብዬ አዝዤሃለሁ።


አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር የተገደለ ሰው በሜዳ ወድቆ ቢገኝ፥


ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የአማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንን አትርሳ።


አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፥ ርስት አድርጌ በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን ፍርዴንም ሁሉ እነግርሃለሁ።


አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም በዕድሜአችሁ ሁሉ ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉአት ዘንድ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዛት ትእዛዝና ሥርዓት ፍርድም ይህች ናት።


እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ እወቅ።


跟着我们:

广告


广告