Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ የአርጎብን ምድር ሁሉ ወሰደ፤ ይችንም የባሳንን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በስሙ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር፣ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ወሰን ድረስ የሚገኘውን መላውን የአርጎብ ምድር ወሰደ፤ ምድሪቱም በስሙ ተጠራች፤ ከዚሁ የተነሣ ባሳን እስከ ዛሬ ድረስ ሓቦት ኢያዕር ትባላለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የምናሴ ልጅ ያኢር፥ ባሳንን እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ፥ የአርጎብን ግዛት ሁሉ ወሰደ፥ ይችንም የባሳን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በሚጠራበት የያኢር መንደሮች ብሎ ጠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከምናሴ ነገድ ወገን የሆነው ያኢር መላውን የአርጎብ ምድር ወረሰ፤ ይህችውም እስከ ገሹርና እስከ ማዕካ ጠረፍ የምትደርሰው ባሳን ናት፤ መንደሮቹንም በእርሱ ስም እንዲጠሩ አደረገ፤ ስለዚህ እነርሱ የያኢር መንደሮች ተብለው እስከ ዛሬ ይጠራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የም​ናሴ ልጅ ኢያ​ዕር እስከ ጌር​ጋ​ሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ች​ንም የባ​ሳ​ንን ምድር እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በስሙ አው​ታይ ኢያ​ዕር ብሎ ጠራ።

参见章节 复制




ዘዳግም 3:14
14 交叉引用  

የአሞን ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደተጠሉ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከሶርያውያን ከቤትሮዖብና ከሱባ ሀያ ሺህ እግረኞች፥ ከመዓካ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎች፥ ከጦብም አሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


አቤሴሎም ግን ኮብልሎ ወደ ጌሹር ንጉሥ ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ። ዳዊትም ሁልጊዜ ለልጁ ያለቅስ ነበር።


ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፥ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም ይዞ መጣ።


የኢያዕር ሰውም ዒራስ ለዳዊት አማካሪ ነበረ።


የአሮዳዊው የአራር ልጅ አምናን፥ የማዕካታዊው ልጅ የአሐስባይ ልጅ ኤሌፋላት፥ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤልያብ፥


ሁለተኛውም የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረች ከአቢግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።


የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።


የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮችዋን ወሰደ፥ የኢያዕርም መንደሮች ብሎ ጠራቸው።


ከገለዓድም የቀረውን የዐግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተቆጠረች።


በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ አንድም ያልወሰድነው የለም፤ በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አገር ሁሉ፥ ስድሳ ከተሞችን ወሰድን።


ሰልካን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ።


የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላወጡም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።


跟着我们:

广告


广告