Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 24:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ማንም ሰው ከእስራኤል ልጆች ከወንድሞቹ አንዱን ሰርቆ እንደ ባሪያ ሲያደርግበት ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ያ ሌባ ይሙት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባሪያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፣ ፈንጋዩ ይሙት። ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “እስራኤላዊ ወገኑን አፍኖ በመውሰድ ባሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትና ወይም ለሌላ ሰው በባርነት አሳልፎ የሚሸጠው ማንም ሰው በሞት ይቀጣ፤ በዚህም ዐይነት ክፉ ነገርን ታስወግዳላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ማንም ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰ​ር​ቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰ​ረ​ቀ​ውን ሰው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ።

参见章节 复制




ዘዳግም 24:7
11 交叉引用  

የድሀ አድጎቹን አህያ ይነዳሉ፥ የመበለቲቱን በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ።


ድሀ አደጉን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ፥ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ።


ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።


ያዋንና ቶቤል ሞሳሕም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ የሰዎችን ነፍሳትና የናሱን ዕቃ ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።


የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቍቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥


እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ።


በወንድሙ ላይ ያደርገው ዘንድ ያሰበውን በእርሱ ላይ ትመልሱበታላችሁ፤ እንዲሁም ከአንተ መካከል ክፋቱን ታስወግዳለህ።


የሰውን ነፍስ እንደ መውሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይውሰድ።


ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።


跟着我们:

广告


广告