Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 20:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወደ ሰልፍም በቀረባችሁ ጊዜ ከህኑ ይቅረብ ለሕዝቡም እንዲህ ብሎ ይንገራቸው፦

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፣ ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሰራዊቱ ይናገር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፥ ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሕዝቡ ይናገር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጦርነት ከመጀመራችሁ በፊት ካህኑ ወደ ሠራዊቱ ቀርቦ እንዲህ ይበል፦

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወደ ጦር​ነ​ትም በቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ ካህኑ ይቅ​ረብ፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብሎ ይን​ገ​ራ​ቸው፦

参见章节 复制




ዘዳግም 20:2
9 交叉引用  

እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኸሉ። የእስራኤ ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ።”


ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ሰደደ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው።


ጠላቶችህን ለመውጋት በወጣህ ጊዜ፥ ፈረሶችንና ሰረገሎችን ሕዝቡንም ከአንተ ይልቅ በዝተው ባየህ ጊዜ፥ ከግብፅ አገር ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራቸው።


እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፤ ዛሬ ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ትቀርባላችሁ፤ ልባችሁ አይታወክ፥ አትፍሩ፥ አትንቀጥቀጡ፥ በፊታቸውም አትደንግጡ፤


በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ለብሶ ነበርና ሳኦል፦ ኤፉድን አምጣ አለው።


ዳዊትም ሳኦልን፦ ስለ እርሱ የማንም ልብ አይውደቅ፥ እኔ ባሪያህ ሄጄ ያንን ፍልስጥኤማዊ እወጋዋለሁ አለው።


跟着我们:

广告


广告