Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓብን አትጣላ በሰልፍም አትውጋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሞዓባውያን ምድር አንዳችም መሬት ስለማልሰጣችሁ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው፤ ዔርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ ‘የሎጥ ዘሮች የሆኑትን ሞአባውያንን አታስቸግሩ፤ ከእነርሱም ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ የዔርን ከተማ ለእነርሱ መኖሪያ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህም ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁም።’ ”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ እኔ አሮ​ኤ​ርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከም​ድሩ ርስት አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን አት​ጣላ፤ በሰ​ል​ፍም አት​ው​ጋ​ቸው።

参见章节 复制




ዘዳግም 2:9
13 交叉引用  

አሁንም፥ እነሆ! እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ያልፉባቸው ዘንድ ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ፈቀቅ ብለው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፤


ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም። የሞዓብ ኤር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፥ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።


ወደ ዔር ማደሪያ የሚወርድ በሞዓብም ዳርቻ የሚጠጋ የሸለቆች ፈሳሽ።


እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤


ሞዓብም የምድያምን ሽማግሌዎች፦ በሬ የለመለመውን ሣር እንደሚጨርስ ይህ ጭፍራ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ይጨርሳል አላቸው። በዚያን ጊዜም የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ።


የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።


እንዲህም አለው፦ ዮፍታሔ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል የሞዓብን ምድር የአሞንንም ልጆች ምድር አልወሰደም፥


እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፦ በምድርህ እንዳልፍ፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ ብሎ መልክተኞችን ላከ፥ የኤዶምያስም ንጉሥ አልሰማም። እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፥ እርሱም አልፈቀደም።


እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል ሄዱ፥ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፥ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፥ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና የሞዓብን ድንበር አላለፉም።


跟着我们:

广告


广告