Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አምላክህም እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ዳርቻህን ቢያሰፋ፥ ይሰጣቸውም ዘንድ ለአባቶችህ የተናገረውን ምድር ሁሉ ቢሰጥህ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ለአባቶችህ በመሐላ በገባላቸው ቃል መሠረት፣ አምላክህ እግዚአብሔር ወሰንህን ሲያሰፋውና ለእነርሱ በሰጣቸው መሠረት ምድሪቱን ሁሉ ሲሰጥህ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “ለአባቶችህ በመሐላ በገባላቸው ቃል መሠረት ጌታ እግዚአብሔር ወሰንህን ሲያሰፋውና ለእነርሱ በሰጣቸው መሠረት ምድሪቷን ሁሉ ሲሰጥህ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ በመሐላ የተስፋ ቃል በገባላቸው መሠረት ግዛትህን ቢያሰፋልህ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ​ላ​ቸው ዳር​ቻ​ህን ቢያ​ሰፋ፥ ለአ​ባ​ቶ​ችህ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ምድር ሁሉ ቢሰ​ጥህ፥

参见章节 复制




ዘዳግም 19:8
9 交叉引用  

ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።


ሰሎሞንም ከወንዙ ጀምሮ እስከ ግብጽ ዳርቻ እስከ ፍልስጥኤም ድረስ በመንግሥታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብርም ያመጡለት ነበር፤ በዕድሜውም ሙሉ ለሰሎሞን ይገዙ ነበር።


በኢየሩሳሌምም እጅግ ኃያላን ነገሥታት ነበሩ፤ በወንዝም ማዶ ያለውን አገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና ቀረጥን መጥንንም ይቀበሉ ነበር።


ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለሁ።


አሕዛብን ከፊትህ አወጣለሁ፥ አገርህንም አሰፋለሁ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም።


አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ አገርህን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ እንደ ሰውነትህ ፈቃድ ሥጋን ብላ።


ስለዚህ እኔ፦ ለአንተ ሦስት ከተሞችን ለይ ብዬ አዝዤሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告