Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 16:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ ይሁን፤ ሥራን ሁሉ አታድርግበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ለስድስት ቀን እርሾ የሌለበት ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ አድርግ፤ ሥራም አትሥራበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በሚከተሉት ስድስት ቀኖች ደግሞ እርሾ ሳይነካው የተዘጋጀ ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትሰግድ ዘንድ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስድ​ስት ቀን ቂጣ እን​ጀራ ብላ፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን መው​ጫው ስለ​ሆነ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሁን፤ ለነ​ፍ​ስም ከሚ​ሠ​ራው በቀር ሥራን ሁሉ አታ​ድ​ር​ግ​በት።

参见章节 复制




ዘዳግም 16:8
9 交叉引用  

ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ።


ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን ያህል አደረጉ፥ በስምንተኛውም ቀን እንደ ሕጉ የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።


ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።


ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባንን አቅርቡ፤ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን ቍርባን አቅርቡ፤ ዋና ጉባኤ ነው፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት።


በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


跟着我们:

广告


广告