Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘላለምም ወና ትሆናለች፥ ደግሞም አትሠራም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፥ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ ለጌታ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘለዓለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዚያችን ከተማ ሰዎች ሀብት በሙሉ ሰብስበህ በማምጣት በከተማይቱ አደባባይ እንዲከመር አድርግ፤ ከዚያም በኋላ ከተማይቱንና ሀብቱን ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ በእሳት አቃጥለው፤ ዳግመኛም እንዳትሠራ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆና ትቅር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ትሰ​በ​ስ​ባ​ለህ፤ ከተ​ማ​ይ​ቱ​ንም፥ ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በእ​ሳት ፈጽ​መህ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወና ትሆ​ና​ለች፤ ደግ​ሞም አት​ሠ​ራም።

参见章节 复制




ዘዳግም 13:16
13 交叉引用  

ከእንስሳ ጋር የሚረክስ ፈጽሞ ይገደል።


ስለ ደማስቆ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ ደማስቆ ከተማ ከመሆን ተቋርጣለች፥ ባድማና የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።


ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፥ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፥ የኀጥኣንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፥ ከቶ አትሠራም።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።


የተራቈተ ድንጋይ አደርግሻለሁ የመረብም ማስጫ ትሆኛለሽ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አትሠሪም፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፥ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።


በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።


ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አደረጉት።


በዚያን ጊዜም ኢያሱ፦ ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፥ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ ብሎ ማለ።


ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ እስከ ዛሬም ድረስ ድብድባና በረሃ ለዘላለም አደረጋት።


跟着我们:

广告


广告