Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 1:44 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ ንብ እንደምታሳድድም አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 በእነዚያ በተራራማው አገር የሚኖሩት አሞራውያን ሊወጓችሁ ወጡ፤ እንደ ንብ ሰራዊትም ሆነው አባረሯችሁ፤ ከሴይር አንሥቶ እስከ ሖርማ ድረስ አሳድደው መቷችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ እንደ ንብ መንጋ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር ድል ነሷችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 በነዚያ ኮረብታዎች ላይ የሚኖሩ አሞራውያንም መጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ሠራዊታቸውም እንደ ንብ መንጋ ግር ብለው መጥተው እስከ ሆርማ ድረስ አሳደዱአችሁ፤ ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም አገርም ድል አደረጉአችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 በዚ​ያም ተራ​ራማ አገር ይኖሩ የነ​በሩ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ወጥ​ተው ተጋ​ጠ​ሙ​አ​ችሁ፤ ንብ እን​ደ​ም​ት​ነ​ድ​ፍም ነደ​ፉ​አ​ችሁ፤ አሳ​ደ​ዱ​አ​ች​ሁም፤ ከሴ​ይር እስከ ሔር​ማም ድረስ መቱ​አ​ችሁ።

参见章节 复制




ዘዳግም 1:44
7 交叉引用  

በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝምብ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።


በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ አማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፥ መትተዋቸውም እስከ ሔርማ ድረስ አሳደዱአቸው።


እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ፤ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት።


እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፥ በሰባት መንገድ ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ ለምድርም መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።


እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር?


የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን መቱ፥ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው በቁልቁለቱም መቱአቸው፥ የሕዝቡም ልብ ቀለጠ፥ እንደ ውኃም ሆነ።


跟着我们:

广告


广告