Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 1:43 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፤ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 እኔም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁም፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐምፃችሁ፣ በትዕቢታችሁ ወደ ተራራማው አገር ዘመታችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 እኔም ተናገርኋችሁ፥ እናንተ ግን በጌታ ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፥ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 እግዚአብሔር ያለኝንም ለእናንተ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እምቢተኞች ሆናችሁ፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችሁ በትዕቢታችሁ ብዛት ወደ ኮረብታማይቱ አገር ዘመታችሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እኔም ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ተላ​ለ​ፋ​ችሁ፤ በኀ​ይ​ላ​ች​ሁም ወደ ተራ​ራ​ማው አገር ወጣ​ችሁ።

参见章节 复制




ዘዳግም 1:43
8 交叉引用  

እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፥ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፥ እርሱም ተዋጋቸው።


በነጋውም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ ወጥተው፦ እነሆ፥ መጣን፤ እኛ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን አሉ።


እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ሊወጡ ደፈሩ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ አልተነሡም።


የአገር ልጅ ቢሆን ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ አንዳች በትዕቢት የሚያደርግ ሰው እግዚአብሔርን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።


እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ ወደ እርስዋ መውጣትን እንቢ አላችሁ፤


ማናቸውም ሰው ቢኮራ፥ በዚያም አምላክህን እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ለመስማት ባይወድድ፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም ዘንድ ክፋትን አስወግድ፤


跟着我们:

广告


广告