Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከኮሬብም ተጓዝን፥ አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን በታላቁ እጅግም በሚያስፈራ በዚያ ባያችሁት ምድረ በዳ ሁሉ በኩል በተራራማው በአሞራውያን መንገድ ሄድን፤ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር ባዘዘን መሠረት ከኮሬብ ተነሥተን እንዳያችሁት በዚያ ጭልጥ ባለና በሚያስፈራ ምድረ በዳ ዐልፈን፣ በኰረብታማው በአሞራውያን አገር በኩል ወደ ቃዴስ በርኔ መጣን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “ከኮሬብም ወጣን፥ ጌታ አምላካችን እንዳዘዘን በታላቁ እጅግም በሚያስፈራ በዚያ ሁሉ ባያችሁት ምድረ በዳ በኩል በተራራማው በአሞራውያን መንገድ ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን ከሲና ተነሥተን እናንተ ባያችሁት አስቸጋሪ በረሓ በተራራማው በአሞራውያን አገር በኩል አድርገን ወደ ቃዴስ በርኔ መጣን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ከኮ​ሬ​ብም ተጓ​ዝን፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በታ​ላቁ፥ እጅ​ግም በሚ​ያ​ስ​ፈራ በዚያ ባያ​ች​ሁት ምድረ በዳ ሁሉ በኩል በአ​ሞ​ሬ​ዎን ተራራ መን​ገድ ሄድን፤ ወደ ቃዴስ በር​ኔም መጣን።

参见章节 复制




ዘዳግም 1:19
13 交叉引用  

እነርሱም፦ ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጕድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።


የእስራኤልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየጉዞአቸው ተጓዙ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ቆመ።


ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤


በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።


ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።


ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በሰደድኋቸው ጊዜ አባቶቻችሁ እንዲህ አደረጉ።


በሴይር ተራራ መንገድ ከኮሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የአሥራ አንድ ቀን መንገድ ነው።


እኔም፦ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ወደ ተራራማው ወደ አሞራውያን አገር መጣችሁ፤


ተመልሳችሁ ተጓዙ፤ ወደ ተራራማው ወደ አሞራውያን አገር ወደ ድንበሮቹም ሁሉ፥ በዓረባም በደጋውም በቈላውም በደቡብም በባሕርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም እስከ ታላቁ ወንዝም እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።


አምላክህ እግዚአብሔር የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፤ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም።


በምድረ በዳ በጥማት፥ 2 የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ 2 ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ 2 እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።


እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት፥ በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከጭንጫ ድንጋይም ውኃን ያወጣልህን፥


ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ።


跟着我们:

广告


广告