Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህም እግዚአብሔር ክፉ ነገሩን ጠብቆ በእኛ ላይ አመጣ፥ አምላካችን እግዚአብሔር በሚሠራው ሥራ ሁሉ ጻድቅ ነውና፥ እኛም ቃሉን አልሰማንምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፤ እኛም አልታዘዝነውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በሥራህ ሁሉ እውነተኛ ነህ፤ እኛ ግን ስለ አልታዘዝንህ ይህን ሁሉ መከራ አመጣህብን።

参见章节 复制




ዳንኤል 9:14
16 交叉引用  

የእስራኤልም መሳፍንትና ንጉሡ“እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤” ብለው ሰውነታቸውን አዋረዱ።


አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”


በደረሰብንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፥ አንተ እውነት አድርገሃልና፥ እኛም ኃጢአት አድርገናል።


ፈርዖንም ልኮ ሙሴንና አሮንን ጠራ፤ “በዚህ ጊዜ በደልሁ፤ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤም ኃጢያተኞች ነን።


አቤቱ፥ ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?


እንዲህም ይሆናል፥ አፈርሳቸውና ክፉ አድርግባቸው ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው፥ እንዲሁ እሠራቸውና እተክላቸው ዘንድ እተጋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፥ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።


ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።


የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽምና፥ በዚህም ነገር ሁሉ አስቈጥተሽኛልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ እኔ ደግሞ መንገድሽን በራስሽ ላይ አመጣለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ሌላንም ነውር በርኵሰትሽ ሁሉ ላይ አትጨምሪም።


ዘመኑም ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዓይኔን ወደ ሰማይ አነሣሁ፥ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፥ ልዑሉንም ባረክሁ፥ ለዘላለምም የሚኖረውን አመሰገንሁ አከበርሁትም፥ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና፥ መንግሥቱም ለልጅ ልጅ ነውና።


ጌታ ሆይ፥ ጽድቅ ለአንተ ነው፥ እንደ ዛሬም ለእኛ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ ለእስራኤልም ሁሉ በቅርብና በሩቅም ላሉት አንተን በበደሉበት በበደላቸው ምክንያት በበተንህበት አገር ሁሉ የፊት እፍረት ነው።


跟着我们:

广告


广告