Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 8:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አውራውም በግ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንም ወደ ደቡብም በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ፥ አራዊትም ሁሉ ይቋቋሙት ዘንድ አልቻሉም፥ ከእጁም የሚያድን አልነበረም፥ እንደ ፈቃዱም አደረገ፥ ራሱንም ታላቅ አደረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አውራ በጉም ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ። ምንም ዐይነት እንስሳ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም ሊያድን የሚችል አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ አደረገ፤ ታላቅም ሆነ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ያም በግ በቀንዶቹ ለመጐሸም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ ሲቃጣ አየሁ፤ በፊቱ ቀርቦ የሚቋቋመው ወይም ከኀይሉ ማምለጥ የሚችል አውሬ አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ ያደርግ ነበር፤ ይበልጥም እየበረታ ሄደ።

参见章节 复制




ዳንኤል 8:4
18 交叉引用  

የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ሶርያውያንን ትወጋለህ፤’” አለ።


ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።


እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥


በእርሱም ላይ የሚመጣው ግን እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ በፊቱም የሚቆም የለም፥ በመልካሚቱም ምድር ይቆማል፥ በእጁም ውስጥ ጥፋት ይሆናል።


ንጉሡም እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ በአማልክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ ያደርጋል፥ በአማልክትም አምላክ ላይ በትዕቢት ይናገራል፥ ቍጣም እስኪፈጸም ድረስ ይከናወንለታል፥ የተወሰነው ይደረጋልና።


ስለ ሰጠው ታላቅነት ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ በፊቱ ይንቀጠቀጡና ይፈሩ ነበር፥ የፈቀደውን ይገድል፥ የፈቀደውንም በሕይወት ያኖር ነበር፥ የፈቀደውንም ያነሣ፥ የፈቀደውንም ያዋርድ ነበር።


በዚያ ሌሊት የከለዳውያን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ።


እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፥ እንደዚህም፦ ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ ተባለላት።


ወደ አውራውም በግ ሲቀርብ አየሁት፥ እርሱም ተመረረበት፥ አውራውንም በግ መታ፥ ሁለቱንም ቀንዶች ሰበረ፥ አውራውም በግ ሊቋቋመው ኃይል አልነበረውም፥ እርሱም በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፥ አውራውንም በግ ከእጁ ያድነው ዘንድ የሚችል አልነበረም።


በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።


ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፤ 2 ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤ 2 በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን 2 አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤ 2 የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ 2 የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告