Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 8:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዓይኔን አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ቀንዶች የነበሩት አንድ አውራ በግ በወንዙ ፊት ቆሞ ነበር፥ ሁለቱም ቀንዶቹ ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፥ አንዱ ግን ከሁለተኛው ከፍ ያለ ነበረ፥ ታላቁም ወደ ኋላው ወጥቶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዐይኔን አንሥቼ ስመለከት እነሆ፤ ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ በወንዙ አጠገብ ቆሞ አየሁ፤ ቀንዶቹም ረዣዥሞች ነበሩ፤ ከቀንዶቹም አንዱ ከሌላው ይረዝማል፤ የበቀለው ግን ዘግይቶ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚያም ወንዝ ዳር ሁለት ረጃጅም ቀንዶች ያሉት አንድ አውራ በግ ቆሞ ነበር፤ ከሁለቱ ቀንዶች አንደኛው ዘግይቶ የበቀለ ቢሆንም ከሌላው ቀንድ ይረዝም ነበር።

参见章节 复制




ዳንኤል 8:3
25 交叉引用  

ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፉ።


“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እሠራለት ዘንድ አዝዞኛል፤


ምክራቸውንም ያፈርሱ ዘንድ በፋርሱ ንጉሥ በቂሮስ ዘመን ሁሉ እስከ ፋርስ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ መንግሥት ድረስ መካሪዎችን ገዙባቸው።


በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ለባለምዋሎቹና ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ፥ የፋርስና የሜዶን ታላላቆች ሁሉ፥ የየአገሩ አዛውንትና ሹማምት፥ በፊቱ ነበሩ፥


እነሆ፥ ብር የማይሹትን፥ ወርቅም የማያምራቸውን ሜዶናውያንን በላያቸው አስነሣለሁ።


ከባድ ራእይ ተነገረኝ፥ ወንጀለኛው ይወነጅላል አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፥ ትካዜውን ሁሉ አስቀርቻለሁ።


ቂሮስንም፦ እርሱ እረኛዬ ነው፥ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል እላለሁ።


ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ፥ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፥ የእግዚብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።


እነሆም፥ በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ።


ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሣል፥ ከዚያም በኋላ በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሌላ ሦስተኛ የናስ መንግሥት ይነሣል።


ሜዶናዊውም ዳርዮስ መንግሥቱን ወሰደ፥ ዕድሜውም ስድሳ ሁለት ዓመት ነበረ።


ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ኑሮው ተቃናለት።


እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፥ እንደዚህም፦ ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ ተባለላት።


በራእዩም አየሁ፥ ባየሁም ጊዜ በኤላም አውራጃ ባለው በሱሳ ግንብ ነበርሁ፥ በራእዩም አየሁ በኡባል ወንዝም አጠገብ ነበርሁ።


ባየኸው በአውራው በግ ላይ የነበሩ ሁለቱ ቀንዶች እነርሱ የሜዶንና የፋርስ ነገሥታት ናቸው።


ዓይኖቼንም አንሥቼ እነሆ፥ አራት ቀንዶች አየሁ።


ዓይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ።


ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ።


ዓይኖቼንም አንሥቼ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁለት ሴቶች ወጡ፥ ነፋስም በክንፎቻቸው ነበረ፥ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፥ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።


ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራራ መካከል ሲወጡ አየሁ፥ ተራሮቹም የናስ ተራሮች ነበሩ።


በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ መጣ።


እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፥ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው።


ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።


በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


跟着我们:

广告


广告