Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 8:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እኔም ዳንኤል ተኛሁ፥ አያሌም ቀን ታመምሁ፥ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ የንጉሡን ሥራ እሠራ ነበር፥ ስለ ራእዩም አደንቅ ነበር፥ የሚያስተውለው ግን አልነበረም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እኔ ዳንኤል ዐቅሜ ተሟጥጦ ነበር፤ ለብዙ ቀናት ታመምሁ፤ ተኛሁም። ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ወደ ንጉሡ ሥራ ሄድሁ። ባየሁት ራእይ ተደናግጬ ነበር፤ ነገሩም አልገባኝም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እኔ ዳንኤል እጅግ ደከመኝና ሕመም ስለ ተሰማኝ ለብዙ ቀኖች ተኛሁ፤ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ንጉሡ በመደበልኝ ሥራ ላይ ተሰማራሁ፤ በራእዩ እጅግ ተጨነቅሁ፤ ላስተውለውም አልቻልኩም ነበር።

参见章节 复制




ዳንኤል 8:27
12 交叉引用  

እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሬን ዳሰሰኝ፥ የዚያን ጊዜም አፌን ከፍቼ ተናገርሁ በፊቴም ቆሞ የነበረውን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።


እኔም ብቻዬን ቀረሁ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፥ ኃይልም አልቀረልኝም፥ ደም ግባቴም ወደ ማሸብሸብ ተለወጠብኝ፥ ኃይልም አጣሁ።


የዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል አንድ ሰዓት ያህል አሰበ፥ ልቡም ታወከ። ንጉሡም መልሶ፦ ብልጣሶር ሆይ፥ ሕልሙና ፍቺው አያስቸግርህ አለው። ብልጣሶርም መልሶ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠሉህ፥ ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን።


የአማልክት መንፈስ እንዳለብህ፥ እውቀትና ማስተዋልም መልካምም ጥበብ እንደ ተገኘብህ ስለ አንተ ሰምቻለሁ።


የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በአሳቤ እጅግ ተቸገርሁ፥ ፊቴም ተለወጠብኝ፥ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠብቄአለሁ።


እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፥ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፥ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ።


በራእዩም አየሁ፥ ባየሁም ጊዜ በኤላም አውራጃ ባለው በሱሳ ግንብ ነበርሁ፥ በራእዩም አየሁ በኡባል ወንዝም አጠገብ ነበርሁ።


ወደ አውራውም በግ ሲቀርብ አየሁት፥ እርሱም ተመረረበት፥ አውራውንም በግ መታ፥ ሁለቱንም ቀንዶች ሰበረ፥ አውራውም በግ ሊቋቋመው ኃይል አልነበረውም፥ እርሱም በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፥ አውራውንም በግ ከእጁ ያድነው ዘንድ የሚችል አልነበረም።


እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፥ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፥ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


ሳሙኤልም እስኪነጋ ተኛ፥ ማልዶም ተነሥቶ የእግዚአብሔርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙኤልም ራእዩን ለዔሊ መንገር ፈራ።


跟着我们:

广告


广告