Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት ድረስ ነው፥ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱም፣ “እስከ ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ምሽቶችና ማለዳዎች ድረስ ይቈያል፤ ከዚያም መቅደሱ እንደ ገና ይነጻል” አለኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የተጠየቀውም ቅዱስ “የጠዋትና የማታ መሥዋዕት የማይቀርብባቸው ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ቀኖች ይሆናሉ፤ ከዚያን በኋላ ቤተ መቅደሱ ይነጻል” ብሎ ሲመልስለት ሰማሁ።

参见章节 复制




ዳንኤል 8:14
14 交叉引用  

እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራዉ። ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አንድ ቀን።


ጽዮን በፍርድ ከእርሷም የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ።


የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይባላል።


የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኵሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።


የሚታገሥ፥ እስከ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀንም የሚደርስ ምስጉን ነው።


ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፦ ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው፥ የተቀደሰውም ሕዝብ ኃይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል ብሎ ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ።


በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፥ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።


የተነገረውም የማታውና የጥዋቱ ራእይ እውነተኛ ነው፥ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ ስለሚሆን ራእዩን ዝጋ።


መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።


ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል


ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።


ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።


跟着我们:

广告


广告