Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፥ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፥ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፥ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፥ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኀይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፣ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።

参见章节 复制




ዳንኤል 7:7
17 交叉引用  

እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፥ እንደ አደባባይም ጭቃ ረገጥኋቸው፥ ደቀደቅኋቸውም።


በአንገቱ ኃይል ታድራለች፥ ግርማ በፊቱ ይዘፍናል።


በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ እጅግም በረዘመ ተራራ ላይ አኖረኝ፥ በዚያም ላይ በደቡብ ወገን እንደ ከተማ ሆኖ የተሠራ ነገር ነበረ።


የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት፥ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ።


በሌሊት ራእይ አየሁ፥ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፥ ወደ ፊቱም አቀረቡት።


ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ በሌሊት በራእይ አየሁ፥ እነሆም፥ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በታላቁ ባሕር ላይ ይጋጩ ነበር።


እስከ ሰማይም ሠራዊት ድረስ ከፍ አለ፥ ከሠራዊትና ከከዋክብትም አያሌዎችን ወደ ምድር ጣለ፥ ረገጣቸውም።


እርሱም በተሰበረ ጊዜ በእርሱ ፋንታ አራቱ እንደ ተነሡ፥ እንዲሁ ከወገኑ አራት መንግሥታት ይነሣሉ፥ ነገር ግን በኃይል አይተካከሉትም።


ዓይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥


አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።


ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።


መልአኩም አለኝ፦ የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።


ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።


跟着我们:

广告


广告