Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 6:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ንጉሡም አዘዘ፥ ዳንኤልንም የከሰሱ እነዚያን ሰዎች አመጡአቸው፥ እነርሱንና ልጆቻቸውንም ሚስቶቻቸውንም በአንበሶች ጕድጓድ ጣሉአቸው፥ ወደ ጕድጓዱም መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶች ያዙአቸው አጥንታቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በንጉሡ ትእዛዝ፣ ዳንኤልን በሐሰት የከሰሱትን ሰዎች፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋራ አምጥተው፣ በአንበሶቹ ጕድጓድ ውስጥ ጣሏቸው፤ ገና ወደ ጕድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱም፣ አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።

参见章节 复制




ዳንኤል 6:24
13 交叉引用  

በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም በአባቶች አይሙቱ፤” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም።


ሐማንም ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሰቀሉት፥ በዚያም ጊዜ የንጉሡ ቍጣ በረደ።


ዛቡታዮስ የሚባሉትን፥ የሐመዳቱን ልጅ የአይሁድን ጠላት አሥሩን የሐማን ልጆች ገደሉ፥ ነገር ግን ወደ ብዝበዛው እጃቸውን አልዘረጉም።


አስቴርም ወደ ንጉሡ ፊት በገባች ጊዜ በአይሁድ ላይ የተተነኰለው ክፉ ተንኰል በራሱ ላይ እንዲመለስ፥ እርሱና ልጆቹም በግንድ ላይ እንዲሰቀሉ በደብዳቤው አዘዘ።


እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፥ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፥ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እንድትበተኑ አደርጋችኋለሁ።


የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው።


አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።


跟着我们:

广告


广告