30 በዚያ ሌሊት የከለዳውያን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ።
30 በዚያ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ፤
30 በዚያኑ ሌሊት የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ፤
አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በድንገት ይመጡብሻል፥ ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።
ባቢሎን ሆይ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።
ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ፥ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፥ የእግዚብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካዎችዋም እንደ ተያዙ፥ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፥ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።
በሞቃቸው ጊዜ ደስ እንዲላቸው ለዘላለምም አንቀላፍተው እንዳይነቁ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ አሰክራቸውማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
ስለዚህ በምርኮ መጀመሪያ ይማረካሉ፥ ተደላድለው ከተቀመጡትም ዘንድ ዘፈን ይርቃል።